Quantcast
Channel: Ethiopia | AddisNews.net
Viewing all articles
Browse latest Browse all 199

በጎንደር ከተማ በህዝቡ እና የጸጥታ ሃይሎች የተነሳው የተቃውሞ ግጭት ቀጥሏል –በፎቶ እና ቪዲዮ

$
0
0

Ethiopia protest gonder

AddisNews: በጎንደር ከተማ የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በኮሚቴ አባልነት የሚመሩትን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚል የተንቀሳቀሱ የደህንነት አባላት እና የከተማው ህዝብ መካከል በተፈጠረው ግጭት በሁለቱም ወገን የተገደሉ እና የቆሰሉ መኖራቸው እየተዘገበ ነው::

ይህ ዘገባ እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ ከሃያ የማያንሱ ሰዎች በግጭቱ መገደላቸው እየተነገረ ነው::

ከሰው ህይወት በተጨማሪም የከተማው ህዝብ በስልጣን ላይ ላለው የገዢው ፓርቲ ቅርብ እና ደጋፊ ናቸው ያላቸውን ሰላም ባስን ጨምሮ የንግድ መደብሮችን: ሆቴሎችን እና ተሽከርካሪዎችን በእሳት በማቃጠል እና በመሰባበር ተቃውሞውን እየገለጸ ነው::

ይህ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ የተባሉ የማንነት ኮሚቴ አባል ለማሰር በሚሞክሩበት ወቅት የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ በማስነሳቱ  ተፈጠረ በተባለው በዚህ እንቅስቃሴ ከትላንት ጀምሮ ተባብሶ አብዛኛው የጎንደር ከተማ ወጣት የተቃውሞ ድምጹን እያሰማ ይገኛል::

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ግለሰቦች የማንነት ኮሚቴ አባላቱን ለማፈን የተንቀሳቀሱት የጸጥታ ሃይሎች ከትግራይ ክልል የመጡ እንደሆነ እየገለጹ ነው::

በኢሳት ቴሌቭዥን እና በማህበራዊ ድረ-ገጾች በተለጠፉ ምስሎች እንደሚታየው የጸጥታ ሃይሎች ጥይት እየተኮሱም የከተማው ነዋሪ በብዛት ወጥቶ ገዢውን መንግስት በሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ላይ እንደነበር ያሳያል::

ፋናን ጨምሮ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ግጭቱን በኤርትራ የሚታገዙ ሃይሎች እንደፈጠሩት እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የሞከሩትም በትግራይ ሰዎችን የገደሉ ግለሰቦችን እንደሆነ ዘግበዋል

በተያያዘ ዜና የእስራኤል መንግስት የግጭቱን መቀስቀስ በማየት በጎንደር የሚገኙ 23 የስራ አጋዥ ወጣቶችን ወደ አቅራቢያው አየር ማረፊያ እንደወሰደ ጄፖስት የተሰኘው የሃገሪቱ ድረ ገጽ ዘግቧል:: በዚህ ዘገባውም ከማክሰኞ ጠዋት ጀምሮ በአማራ እና ትግሬ ብሄሮች መካከል ግጭት መቀስቀሱን እና ከትግራይ ክልል የመጡ የትግራይ ነጻ አውጪ የጦር አባላት በከተማው በመግባት ግጭት አስነስተዋል ያላቸውን የፖለቲካ መሪዎች እንዳሰሩ በግጭቱም  10 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ጨምሮ ጠቅሷል::በጎንደር እና አካባቢው ሌሎች 6ሺ የሚሆኑ ፈላሻዎች ወደ እስራኤል ለመሄድ በመጠባብቅ ላይ ናቸው::

ግጭቱን አስመልክቶ የአሜሪካ ድምጽ ነዋሪዎችን አነጋግሮ ያዘጋጀውን ዘገባ ያዳምጡ

ይህን የተቃውሞ እንቅስቃሴ እና ግጭት በተመለከተ የሚደረሰንን ተጨማሪ መረጃ እናቀርባለን::

gonder protest 3 gonder protest 5 gonder protest 2 Protest in Gonder in Pictures gonder protest 4 gonder protest 6 gonder protest 8 gonder protest 7

Viewing all articles
Browse latest Browse all 199

Trending Articles