Quantcast
Channel: Ethiopia | AddisNews.net
Viewing all articles
Browse latest Browse all 199

የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ

$
0
0

merkel-ethiopia
የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ
– ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ይወያያሉ
በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት (ቻንስለር) አንገላ መርከል በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ፡፡ ምንም እንኳን መንግሥት ቻንስለሯን በፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ቢጠይቅም፣ መርከል ግን ‹‹በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ውስጥ ንግግር ማድረግ ምንም ለውጥ አያመጣም፤›› በማለት ግብዣውን እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቻንስለሯ ከእሑድ ጀምሮ ሦስት የአፍሪካ አገሮች የሚጐበኙ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ወደ ማሊና ኒጀር ተጉዘው ኢትዮጵያ ሲመጡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ይገናኛሉ፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረትን ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡ ቻንስለሯ አዲስ አበባ ሰኞ አመሻሽ ላይ እንደሚደርሱ፣ አብሯቸውም የጀርመን ፌዴራል ጽሕፈት ቤት ባልረደቦች ብቻ እንደሚመጡ ተገልጿል፡፡ ከቻንስለሯ ጋር ምንም ዓይነት የቢዝነስ ልዑካን የማይመጣ ሲሆን፣ ይህም በሎጂስቲክስ ችግር መሆኑ ታውቋል፡፡ ቻንስለሯ ሰኞ አመሻሽ ላይ ከገቡ በኋላ ማክሰኞ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት አቀባበል የሚደረግላቸው ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ረቡዕ ይገናኛሉ፡፡
ምንጮች ለሪፖርተር፣ ‹‹ቻንስለር መርከል በአገሪቱ በተፈጠረው ተቃውሞ የፀጥታ ኃይሎች ዜጐች ላይ እየወሰዱት ስላለው አላስፈላጊና ከመጠን ያለፈ ኃይል ከመንግሥት ጋር ይወያያሉ፤›› ከዚህም ባለፈ፣ ‹‹በቁጥጥር ሥር በተከፈተ›› የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ላይ ይወያያሉ ብለዋል፡፡ ቻንስለሯ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሚኖራቸው ውይይት ስደተኞችን በተመለከተና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ ተብሏል፡፡
ቻንስለሯ መርከል በአዲስ አበባ ቆይታቸው ወቅት፣ ከተመረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ፣ ቻንስለሯ ስድስት ከሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በጀርመን ኤምባሲ ይወያያሉ፡፡ ሆኖም የውይይቱ አጀንዳንና ተሳታፊዎቹ ማን እንደሆኑ ምንጮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

ቀሪውን ዜና ሪፖርተር ላይ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 199

Trending Articles