የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወሰነው መሰረት መንግስት በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የነበሩ ተከሳሾችን ክስ እያቋረጠ መሆኑ ይታወቃል ።
በዚሁ መሰረትም በዛሬው ዕለት የ101 ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ከነዚህም ውስጥ 56ቱ የግንቦት ሰባት 41ዱ የኦነግ ተባባሪ ተብለው የተከሰሱ ነበሩ።
አራቱ ደግሞ በኃይማኖት አክራሪነትና ሽብር የተከሰሱ ነበሩ።
ከነዚህም ውስጥ ኮነሬል ደመቀ ዘውዴ ጌታቸው አደመ፣ አታላይ ዘርፉ ንግስት ይርጋና ተሻገር ወልደ ሚካኤል ይገኙበታል፤
በተያያዘ ዜና በተለያየ ወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸው 18 ሰዎች በይቅርታ ቦርድ ጉዳያቸው እነዲታይና በርዕሰ ብሔሩ ጸድቆ እንዲፈቱ ተወስኗል።
ከነዚህም ውስጥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞና አሳምነው ጽጌ ይገኙበታል።