Quantcast
Channel: Ethiopia | AddisNews.net
Viewing all articles
Browse latest Browse all 199

ኢትዮ ቴሌኮም በስልክ አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ አደረገ

$
0
0

ethiotelecom new price reduction 2018

ኢትዮ ቴሌኮም በስልክ አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ አደረገ
ethiotelecom new price reduction 2018

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 16 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በስልክ አገልግሎት የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ በሰጠው መግለጫ፥ ተቋሙ በስልክ አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የ43 በመቶ፣ የስልክ ድምፅ ላይ የ40 ከመቶ እንዲሁም አጭር የሞባይል የፅሁፍ መልዕክት ላይ የ43 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ገልጿል።

የታሪፍ ቅናሹ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም ነው የገለጸው።

የታሪፍ ቅናሹን ተከትሎም በደቂቃ 83 ሳንቲም የነበረው የሞባይል ስልክ ጥሪ አገልግሎት ወደ 50 ሳንቲም ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

ከዚህ ባለፈም ቀደም ሲል በሜጋ ባይት 35 ሳንቲም የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት 43 በመቶ ቅናሽ ተደርጎበት በሜጋ ባይት ወደ 23 ሳንቲም ዝቅ ብሏል።

በአጠቃላይ በሞባይል ኢንተርኔት ፓኬጆች ላይ ደግሞ ከ33 እስከ 44 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።

በሞባይል እና መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይም እስከ 54 በመቶ ቅናሽ መደረጉም ተገልጿል።

የብሮድባንድ ሲም ካርድ ሽያጭ ለጊዜው የተቋረጠ ሲሆን፥ በቀጣይ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ባንኮች፣ ሆቴሎች እና ሱፐርማርኬቶች ጋር አጋርነት በመፍጠር የብሮድባንድ ሲም ካርድ ሽያጭ እንዲያከናወን ይደረጋልም ነው ያለው።

MOBILE VOICE SERVICE 40% OFF

MOBILE INTERNET SERVICE 43% OFF

BROADBAND INTERNET 54% OFF

MOBILE M2M SERVICE 41% OFF

MOBILE SMS SERVICE 43% OFF

Ethiotelecom-Tariff-Reduction-on-MOBILE-VOICE-SERVICE-40-OFF MOBILE INTERNET SERVICE 43% OFF BROADBAND INTERNET 54% OFF MOBILE M2M SERVICE 41% OFF Ethio telecom MOBILE SMS SERVICE 43% OFF

ዝርዝር የዋጋ ቅናሹን እዚህ ማጣቀሻ ላይ ይመልከቱ

 

http://www.ethiotelecom.et/tariff-reduction-september-2018/

Tariff Reduction


Viewing all articles
Browse latest Browse all 199

Trending Articles